News and Updates News and Updates

የኢትዮጵያን ወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድን ለማስተዳደር ስምምነት ተደረገ

የኢትዮጵያን ወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድን ለማስተዳደር ስምምነት ተደረገ

መንግስት የወጣቶችን ተሳትፎ ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ በመተግበር ላይ እንዳለ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ የፈደራል መንግስት የወጣቶችን ስራ አጥነት ለማቃለል የ10 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ያቋቋመ ሲሆን፣ በ2009 በጀት ዓመት 5 ቢሊዮን  ብር ለፈንዱ ካፒታል ክፍያ የሚሆን በጀት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት  አጽድቋ ፡፡ የቀረው 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ደግሞ በ2010 በጀት ዓመት የሚከፈል መሆኑ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድን ለማስተዳደር የኢፌድሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ የብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድሮች ፋይናንስ ቢሮዎችና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግንቦት 5 ቀን በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በተዘጋጀ መድረክ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

ፈንዱን ለማስተዳደር የሚያስችል አዋጅ የተዘጋጀ ሲሆን እያንዳንዱ ክልል የሚኖረውን ድርሻ እና ጥቅም ላይ የሚውልባቸውን  ደንቦችና ሁኔታዎች የመወሰን እንዲሁም የፈንዱን አጠቀቀም በበላይነት የመምራት ስልጣን ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሰጥቷል፡፡ አዋጁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈንዱን እንዲያስተዳድር ሃላፊነት ሰጥቶታል፡፡

በቀጣይ በአዋጁ ላይ ተጨማሪ ውይይትና ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡