News and Updates News and Updates

News Archive News Archive

Back

በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ላይ ከሚኒስትሮች ጋር ምክክር ተደረገ

በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ላይ ያተኮረ  የምክክር መድረክ በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ሚኒሰተሮች ጋር በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር አዘጋጅነት ተካሄደ፡፡ ስልጠናው በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚስተሮች ሲሰጥ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሆን ከተለያዩ ሚኒስትር መ/ቤቶች ከ21 በላይ የሚሆኑ ሚኒስተሮች እና ኃላፊዎች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  የገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር አብረሃም ተከስተ የምክክር መድረኩ ያሰፈለገበት ዋነኛ አላማ በመንግስት የፊስካል ፖሊሲ፣ የፋይናንስ አስተዳደርና የውጭ ሃብት አሰባሰብ ስርዓት ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖረን በማደረግ እንደ ሃገር ለያዝነው ዓላማ ሁላችንም  የሚጠበቅብንን ሚና እንድንጫወት ይረዳናል ብለዋል፡፡

ዕርዳታና ብድር ድህነትን ለመቀነስ ብሎም ህብረተሰቡን በስፋት ተጠቃሚ በማደረግ በኩል ያለው ሚና ቀላል የማይባል ነው፤ በዚህም ዕድገትና ልማት ለማምጣት ከማሰቻል ባለፈ ጫናን በማያስከትል መልኩ መሆን እንዳአለበት በገንዘብና ኢኮኖሚና ትብብር የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ሪፎርም ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር አቶ ሙሳ መሀመድ ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም ዳይሪክተሩ በማንኛውም ሁኔታ  ከእርዳታና ብድር በፊት በሃገር ውስጥ ገቢ ለመሸፈን ጥረት እንደሚደረግ ጠቅሰዋል ፡፡

 

በውይይቱ ወቅት ከፕሮግራም በጀት ጋር ተያያዞ የተሰተዋሉ ችግሮች የተነሱ ሲሆን የፕሮግራም በጀት ውጤታማነት አለመገምገምና አለመከታተል፣ ከፀደቀው በጀት ውጭ ከፍተኛ የሆነ የበጀት ዝውውርና የተጨማሪ በጀት ጥያቄዎች፣ የመንግስት ግዢ ስርዓትን አለመከተልና በእቅድ አለመመራት፣ ለመንግስት ንብረት አስተዳደር የሚሰጠው ትኩረት እጅግ ደካማ መሆንና ደጋፊ የስራ ክፍሎችን ከሌላ የስራ ክፍሎች ጋር እኩል  አደርጎ አለማየት ዋንኞቹ ናቸው፡፡

ከሚስተሮችም ብዙ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከነሱ ውስጥም አደረጃጀትን አስመልክቶ ማለትም በአንዳንድ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ፣ ግዢ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት በአንድ ዳይሪክተሮች ስር መሆን በዚህም ለክትትልና ግምገማ አስቸጋሪ መሆን፣ፕርፎርማ የሚሰበስበው፣የሚገዛውና የሚከፍተው አንድ አካል መሆን፣ በበጀት ዝውውር ጊዜ ሳይታሰብ የሚያስፈልጉ ግዢዎች መኖርና ሌሎችም እንዴት መስተናገድ እንዳለባቸው በጥያቄ መልክ ተነስተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በተነሱ ጥያቄዎች መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን መፍትሄ ተብለው ከተቀመጡት ውስጥ በህጉ መሰረት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ የግዢን ስርኣትን በእቅድ እንዲመራ ማደረግ ፣ የፕሮግራም በጀት ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣ በተሠጠው በጀት ስራውን ማከናወን ይገኛሉ፡፡ ምክክሩ ለግማሽ ቀን የተካሄደ ነበር፡፡